የጽ/ቤቱ ሥልጣንና ተግባር

  1. ኢንተርፕራይዞችና አምራች ኢንዱስትሪዎች ማምረቻ፣ ማሳያ ፣ መሸጫ ሼድና ህንጻ መገንባት እንዲችል ከሚመለከተው አካል የለማ መሬት ይረከባል፤ እንዲሁም ካርታ የሌላቸው ነባር ይዞታዎችን እና አዲስ የሚሰጡ ቦታዎችን ካርታ እንዲሰራላቸው ያደርጋል፤
  2. ለአዳዲስ የመስሪያ ቦታ ግንባታ አዳዲስ የዲዛይን ስራዎች እንዲከናወኑ ዲዛይን ከሚያዘጋጀው አካል ጋር በጋራ የዲዛይን ስራ እንዲሰራ ያደርጋል፤
  3. ለኢንተርፕራይዝ እና ለአምራች ኢንዱስትሪ የሚውል የመስሪያ ቦታ ከሥራና ክህሎት ቢሮ እና ከኢንዱስትሪ ልማት ቢሮ ፍላጎት ይቀበላል፤ ይደለድላል፤ በከንቲባው ያፀድቃል፤
  4. ኢንተርፕራይዞችና አምራች ኢንዱስትሪዎች የሚጠቀሙባቸውን የማምረቻ ፣ ማሳያ ፣ መሸጫ ሼዶች ፣ ህንፃዎች በኢንዱስትሪ መንደሮች ፣ በክላስተር ማዕከላትና በገበያ ማዕከላት በማደራጀት ያስገነባል የመሰረተ ልማት አውታሮችም እንዲሟላላቸው ያደርጋል፤
  5. ቀድመው የተገነቡትንም ሆነ አዲስ የሚገነቡ የመስሪያ ቦታ ማዕከላትን ስታንዳርድ ያወጣል፣ ሲፀድቅ ይተገብራል፣ ይቆጣጠራል፤
  6. የመስሪያ ቦታ ተጠቃሚዎች ለሆኑ ኢንተርፕራይዞችና አምራች ኢንዱስትሪዎች የማምረቻ ፣ማሳያ እና መሸጫ ቦታ በውል ያስተላልፋል፤ የመጠቀሚያ ኪራይ በወቅቱ እንዲሰበሰብ ያደርጋል፡፡
  7. በመንግስትና መንግስታዊ ባልሆኑ ድርጅቶች ለኢንተርፕራይዞችና አምራች ኢንዱስትሪዎች አገልግሎት እንዲውሉ የተዘጋጁ ወይም የሚዘጋጁ የመስሪያ ቦታዎችን ያስተዳድራል፤ ይቆጣጠራል፤
  8. የመስሪያ ቦታ አሰጣጥ እና ማስተላለፍ የአሰራር ሥርዓት ጥናት ያቀርባል፤ ሲፀድቅ ተግባራዊ ያደርጋል፤
  9. ዕድሳት እና ጥገና የሚያስፈልጋቸው መስሪያ ቦታዎችን በጥናት በመለየት የእድሳት እና የጥገና ስራ ያከናውናል፤
  10. በህገ-ወጥ መንገድ የማምረቻ፣ ማሳያና መሸጫ ማዕከላት ተላልፈው ሲገኙ የተላለፈላቸውንም ሆነ የሚያስተላልፉ አካላት ላይ ክትትል ቁጥጥር በማድረግ እርምጃ ይወስዳል ወይም እንዲወሰድ ያደርጋል፤
  11. የመስሪያ ቦታዎች ሲተላለፉ ተጠቃሚዎች ከተዋዋሉበት የስራ ዘርፍ አላማና ተግባር ውጪ እንዳያውሉ ይከታተላል፤ ይቆጣጠራል፤ አውለው ሲገኙም የማስተካከያ እርምጃ ይወስዳል፤
  12. በመስሪያ ቦታ ልማትና አስተዳደር ዙሪያ የሚያጋጥሙ ችግሮችን ይለያል፤ የአካባቢ ተፅዕኖ ግምገማ እንዲካሄድ ያደርጋል፤ ውጤቱንም ተግባር ላይ ያውላል፤
  13. የክላስተር ማዕከላት ልማት ከኢንዱስትሪ ልማት ፖሊሲ ጋር የተጣጣመ እና ወቅታዊ መሆኑን በየጊዜው ያረጋግጣል፤ እንደአስፈላጊነቱ በመፈተሽ እንዲስተካከል የውሳኔ ሀሳብ ያቀርባል፤ ተግባር ላይ ያውላል፤ አፈፃፀሙን ይከታተላል፤
  14. በመስሪያ ቦታ ውስጥ የሚገኙ ኢንተርፕራይዞችና አምራች ኢንዱስትሪዎች በመስሪያ ቦታ ልማትና አስተዳደር ተግባራት ላይ አጋዥ ሊሆኑ የሚችሉ ልዩ ልዩ ኮሚቴዎች ያደራጃል፤
  15. ለሚያደራጃቸው ኮሚቴዎች መተዳደሪያ ደንብ ያወጣል፤የአፈፃፀም ማኑዋል ያዘጋጃል፤ተግባርና ኃላፊነታቸውን በማሳወቅ ውጤታማ እንዲሆኑ አስፈላጊውን ድጋፍና ክትትል ያደርጋል፡፡
  16. በግል ፣ በመንግስትና መንግስታዊ ካልሆኑ ድርጅቶች ጋር ትስስር በመፍጠር ለኢንተርፕራይዞችና ለአምራች ኢንዱስትሪዎች የመስሪያ ቦታዎች እንዲገነቡ ድጋፍ እንዲያገኙ ሁኔታዎችን ያመቻቻል፣ የአሰራር ስርዓት ይዘረጋል፣ ተፈፃሚነቱን ያረጋግጣል፤
  17. ኢንተርፕራይዞችና አምራች ኢንዱስትሪዎች የመስሪያ ቦታዎችን ችግሮች በጥናት በመለየት መፍትሄ እንዲያገኙ ያደርጋል፤ ምርጥ ተሞክሮዎችን ከሀገር ውስጥ እና ከውጭ ሀገር ለይቶ ያጠናል፣ ይቀምራል፣ ይተገብራል፣ ውጤታማነቱን ይከታተላል፤
  18. ነባር የመስሪያ ቦታዎችን እና አዲስ የሚገነቡ መስሪያ ቦታዎችን በክላስተር ጽንሰ ሀሳብ መሰረት ያደራጃል፣ ተግባር ላይ ያውላል አፈፃፀሙን ይከታተላል፤
  19. በመስሪያ ቦታ ማስተላለፍ እና አስተዳደር ዙሪያ የሚቀርቡ ቅሬታና አቤቱታዎችን ምላሽ እንዲጣቸው ያደርጋል፤
  20. ክፍትና አዲስ የተገነቡ የመስሪያ ቦታዎችን መረጃ በየጊዜው በማጣራት ለከንቲባው ያሳውቃል፤
  21. ለመካከለኛ እና ለከፍተኛ ኢንተርፕራይዞች እና አምራች ኢንዱስትሪዎች አገልግሎት የሚውሉ የኢንዱስትሪ ፓርኮችን በስታንዳርድ መሰረት ያስገነባል፣አስተዳደራዊ ሥራውን በተመለከተ የአሰራር ሥርዓት ያጠናል ወይም ያስጠናል፤ ሲፀድቅ ተግባራዊ ያደርጋል፡፡