የጽ/ቤቱ ኃላፊ መልእክት
በከተማችንን ብሎም በክ/ከተማችን የሚታየውን ድህነትና ስራ አጥነት ለመቀነስ ለአብዛኛው የሕብረተሰብ ክፍል በተለይም ሴቶችንና ወጣቶችን በጥቃቅን እና አነስተኛ ኢንተርፕራይዝ በማደራጀት የስራ እድል እየተፈጠረላቸዉ ይገኛል፡፡ ይሁን እንጂ በተለይ የማምረቻ፣ የመሸጫ እና የማሳያ ቦታ አቅርቦት በሚፈለገው ደረጃ እና ፍጥነት ለኢንተርፕራይዞች ማቅረብ አለመቻሉ እንዲሁም ተሰርተው የቀረቡ የመስሪያ ቦታዎች የሚገነቡባቸው ቦታዎች ምቹ አለመሆን፣ የግንባታ ጥራት መጓደልና መጓተት፤ መሰረተ ልማት ያልተሟላላቸው መሆናቸው ከዘርፉ የሚጠበቀውን ውጤት በሚፈለገው ደረጃ ማድረስ አልተቻለም፡፡
ስለሆነም በክፍለ ከተማው የሚታየውን የማምረቻ፣ማሳያ እና መሸጫ ቦታ ችግር ለመቅረፍ የተለያዩ መንግስታዊ ተቋማትን በማሳተፍ አስፈላጊውን ስትራቴጂ በመንደፍ ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ ይገኛል፡፡ የመስሪያ ቦታ ልማት እና አስተዳደር ጽ/ቤት የመስሪያ ቦታዎችን በማልማት እና በማስተዳደር በዘርፉ ያለውን የመስሪያ ቦታዎች ልማት እና አስተዳደር ችግሮች...... ተጨማሪ ያንብቡ
ፍጹም ግረፌ ገ/ህይወት , የቂርቆስ መስሪያ ቦታዎች ልማትና አስተዳደር ጽ/ቤት ኃላፊ